#Ethiopia | በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የተጠረጠረውን የግዥ ብልሹ አሰራር ለማጣራት ሦስት አመራሮች ከሃላፊነት ታገዱ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ በፕሮግራም በጀት የተፈጸመን ንብረት ግዥ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያና በመገናኛ ብዙሃን ሲሰራጭ የቆየውን መረጃ ክልሉ በቅርበት ሲከታተለው መቆየቱን አስታውቋል።
የመንግስት አካላቱ ህዝባዊ ሀብት ለታለመለት አላማ ብቻ መዋሉን ማረጋገጥ ሃላፊነታቸው በመሆኑ ጥቆማውን በከፍተኛ ሃላፊነት ተቀብለው ወደ ምርመራ መግባታቸውን ገልጸዋል።
ለጉዳዩ በተሰጠው ትኩረት መሰረት አሰራሩንና ህጋዊነቱን የሚያጣራ የፍትህ፣ የኦዲት እና የፀረ ሙስና አካላትን ያካተተ ቡድን ተደራጅቶ ስራ ጀምሯል።
ከዚህ ጎን ለጎን ማጣራቱ ተጠናቆ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እስኪወሰድ ድረስ በጉዳዩ የተጠረጠሩ ሦስት አመራሮች ከሃላፊነታቸው እንዲታገዱ ተደርጓል።
ምርመራው እንደተጠናቀቀ የመንግስትና የህዝብ ሀብት ባባከነ ማንኛውም አካል ላይ የማያዳግም እርምጃ የሚወሰድ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ አቋም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመልክቷል።
ክልሉ ለህዝቡ ንቁ ተሳትፎ ምስጋና በማቅረብ በቀጣይም ብልሹ አሰራሮችን በመጠቆም እና መረጃ በመስጠት ትብብሩን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።
በሌላ በኩል የፌዴራል የሥነምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በክልሉ ጤና ቢሮ ለእናቶችና ህጻናት ጤና በተመደበ በጀት ውድ ስልኮች ተገዝተዋል በተባለው ጉዳይ ላይ የሚደረገው የማጣራት ሂደት ነጻና ገለልተኛ ሆኖ በእውነተኛ ማስረጃ ላይ ብቻ መመስረት እንዳለበት አሳስቧል።
ኮሚሽኑ አክሎም የምርመራው ውጤት ለህዝብ ይፋ በመደረግ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርሆች ሊዳብሩ እንደሚገባ ገልጿል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#southwestethiopia #corruption #ethiopianews #healthsector #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.