#Ethiopia | አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለ500 ተማሪዎች የሚሆኑ 6 ሺህ ደብተሮችን ከመለገሱ ባሻገር ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች የ700 ሺህ ብር የገንዘብ እርዳታ አደረገ።
በደብረ ብርሃን ከተማ በተካሄደው የውይይትና የእውቅና ፕሮግራም ላይ የተቋሙ ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳው ሃይሉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ተቋሙ የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ ለተሳታፊዎች አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ተቋሙ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ከ15.9 ሚሊዮን ብር በላይ ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በድጋፍ መልክ መስጠቱን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተፈራ ወንድምአገኘሁ ገልጸዋል።
በጥቅምት ወር 2015 ዓ ም በ21.6 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ስራ የጀመረው ተቋሙ በአሁኑ ወቅት ጠቅላላ ካፒታሉን ከ612 ሚሊዮን ብር በላይ ማድረስ ችሏል:: ከዚህ በተጨማሪም አጠቃላይ የሀብት መጠኑን ከ4.8 ቢሊዮን ብር በላይ በማድረስ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ከግብር በፊት ከ218 ሚሊዮን ብር በላይ ማትረፍ ችሏል።
በአሁኑ ወቅት ተቋሙ 55 ቅርንጫፎች ከፍቶ ከ270 ሺህ በላይ ደንበኞችን በማፍራት ከ3.9 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ሰብስቧል። በሌላ በኩል ከ23 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ደንበኞች ከ5 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር አሰራጭቷል።
የውይይት መድረኩ ለተቋሙ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት የእውቅና ሰርተፊኬት በመስጠት እንዲሁም የተዘጋጁትን የገንዘብና የዓይነት ድጋፎች ለተጠቃሚዎች በማስረከብ ተጠናቋል።
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ
ስኬትን በተግባር!
#akufada #microfinance #charity #debrebirhan #ethiopianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.