#Fastmereja I ቀደም ሲል “ያሥሚን ጀማል ኮንስትራክሽን” በሚል ስያሜ ይታወቅ የነበረው ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ፣ አዲሱን የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለደንበኞቹ እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ልዩ የበዓል ቅናሽ ማዘጋጀቱን ገለጸ።
የኮምፓስ ፕሮፐርቲስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኑረዲን መሐመድ እንደገለፁት፣ በቦሌ አትላስ እና በካዛንቺስ የሚገነቧቸውን አዳዲስ ፕሮጀክቶች ለሽያጭ ማቅረቡን ገለፀዋል።
አቶ ኑረዲን አክለዉም በቦሌ አትላስ ሳይት የሶሪንግ (የመደገፊያ) ሥራ መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን፣ በካዛንቺስ ደግሞ 5 የቤዝመንት ደረጃዎች ተጠናቀው ህንፃው ግራውንድ ፍሎር ላይ መድረሱ በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል።
ለሽያጭ የቀረቡት የመኖሪያ አፓርትመንቶች እና የንግድ ሱቆች ሲሆኑ፣ የመኖሪያ ቤቶቹ ስፋት ከ55 ካሬ ሜትር studio እስከ 165 ካሬ ሜትር የሦስት መኝታ ክፍል እንደሚሸፍኑ የተገለፀ ሲሆን የካሬ ሜትር መነሻ ዋጋም ከብር 80,500 የሚጀምር ሲሆን፣ የቀረበው እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ቅናሽ እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንደሚቆይ ተገልጿል።
ድርጅቱ ደንበኞቹን ከዋጋ ንረት ለመጠበቅ የ”ዋጋ ዋስትና” (Price Protection) አሰራር መዘርጋቱን የገለጸ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት በግንባታ ወቅት የገበያ የምንዛሬ ጭማሪም ሆነ የዕቃዎች ዋጋ መወደድ ቢከሰት ደንበኞች በተዋዋሉበት የኢትዮጵያ ብር መጠን ብቻ ክፍያቸውን አጠናቀው በጊዜው ቤታቸውን እንደሚረከቡ አስታውቋል።
በተጨማሪም ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ የማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በአንድ የበጎ አድራጎት ተቋም እና በሦስት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ (ሞደስ) ድጋፍ እንደሚያደርግ የገለጸ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት በሀገሪቱ የሪል ስቴት ዘርፍ ከግንባር ቀደም 5 ተቋማት ተርታ ለመሰለፍ ራዕይ ሰንቆ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።



Source: FastMereja









No comments yet.