የኢራን ተመራማሪዎች በብርሃን አማካኝነት የካንሰር ሕዋሳትን የሚያጠፋና 80% ውጤታማ የሆነ ስማርት “ጄል” ሰሩይህ “ስማርት ሃ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የኢራን ተመራማሪዎች በብርሃን አማካኝነት የካንሰር ሕዋሳትን የሚያጠፋና 80% ውጤታማ የሆነ ስማርት “ጄል” ሰሩ
ይህ “ስማርት ሃይድሮጄል” (ፈሳሽ ቅባት) የጡት ካንሰር ዕጢዎችን በጥንቃቄ ኢላማ በማድረግ ለማከም የኬሞቴራፒ እና በብርሃን ላይ የተመሠረተ ሕክምናን ያጣመረ ነው።
ጄሉ ከተፈጥሯዊና ከሰውነት ጋር ተስማሚ ከሆነ “ካይቶሳን” ከተባለ ንጥረ ነገር የተሠራ ነው፡፡
ስፑትኒክ እንደዘገበው መድኃኒቱን በተቆጣጠረ ሁኔታ የሚለቅ ሲሆን፣ የሌዘር ብርሃን ሲያርፍበት ይነቃቃል፡፡
በተለየ ሁኔታ የካንሰር ሕዋሳትን የሚጎዱ የኦክሲጅን ውህዶችን ያመነጫል፡፡
የተደረጉት ሙከራዎች እንደሚያሳዩት፣ ጄሉ ጤናማ ሕዋሳትን ሳይነካ ከ80% በላይ የሚሆኑትን የጡት ካንሰር ሕዋሳት ማጥፋት ችሏል፡፡
ይህ አቀራረብ ከተለመዱት የጡት ካንሰር ሕክምናዎች በተሻለ፣ አነስተኛ ጉዳት የሚያስከትል እና ቀጥተኛ ዒላማውን ብቻ የሚያጠቃ አማራጭ ሊሆን ይችላል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2