#Ethiopia | የቤላ ፉትሳል ውድድር የ2018 ዓ.ም አሸናፊ የሆነው የሽሮሜዳ እግር ኳስ ቡድን በሜዳ ላይ ላሳየው ድንቅ የቡድን ስራ እና የማይበገር መንፈስ የእራት ግብዣ እና የማበረታቻ ሽልማት ተደረገለት።
የሮሚና ባለቤት አቶ ሚካኤል ግርማ ያዘጋጁት ይህ የምስጋና እና የእውቅና ምሽት ለተጫዋቾቹ ከፍተኛ መነቃቃትን የፈጠረ ነበር።
በስነ ስርዓቱ ላይ በውድድሩ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የቡድኑ ተጫዋቾች የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል።
በዚህም መሰረት፡
* በሃይሉ ግርማ (አመለ ሸጋው)፡
የቡድኑ የተከላካይ አማካይ እና ዋና ምሰሶ በመሆን ላሳየው አስደናቂ ብቃት የ100,000 ብር ሽልማት እና የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች እውቅና አግኝቷል።
* ልባርጌ ስዩም፡
በሜዳ ላይ ባሳየው ከፍተኛ ቁርጠኝነት፣ ትጋት እና ድንቅ እንቅስቃሴ የ50,000 ብር ሽልማት ተበርክቶለታል።
* ቶማስ ቶይቶ (ሮዛ)፡
በማራኪ አጨዋወቱ እና በስፖርታዊ ጥበቡ የ30,000 ብር ሽልማት በተወካዩ በኩል ተረክቧል።
በተጨማሪም በምሽቱ ልዩ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት በETFC 02 በ63 ኪሎ ግራም ምድብ የቦክስ ሻምፒዮኑ አትሌት አብርሃም አለም የ100,000 ብር የድል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የቡድኑ አባላት እና ደጋፊዎች ለተደረገላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል፣ ክብር እና ድጋፍ ለሮሚና ባለቤት አቶ ሚካኤል ግርማ ያላቸውን የከበረ ምስጋና እና መልካም ምኞት ገልጸዋል።
#Shiromeda #BellaFutsal #Romina #Boxing #EthiopianSport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen








No comments yet.