#Ethiopia | ለ20 ዓመት ያሳደገችውን ሴት አስታውሶ በፍቅር የተሰናበተው አንበሳ ብዙዎችን ስሜታዊ አድርጓል።
ይህ አንበሳ እንደ እናት ሆና ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ስትንከባከበው የነበረችውን ሴት የሰጣት ፍቅር ብዙዎችን እንዲገረሙም አድርጓል።
ታማሚው አንበሳ ሕይወቱ ከማለፉ በፊት ስትንከባከበው የነበረችውን ሴት የመጨረሻው የፍቅር ሰላምታውን ሰጥቶ ተሰናብቷታል።
ጁፒተር በመባል የሚጠራው ይህ አንበሳ በኮሎሚቢያ የእንስሳት እንክብካቤ መስጫ ማዕከል ከልጅነቱ ጀምሮ ሲጠበቅ ቆይቷል።
ጁፒተር ወደ ማዕከሉ የመጣው እናቱ ከተገደለች በኋላ ገና በሕፃንነቱ ነበር።
ከልጅነቱ ጀምሮ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ስትንከባከበው የነበረችው ይህችው ሴት ብቻ እንደነበረች ተገልጿል።
ጁፒተር አና ጁሊያን ሲያያት በደስታ እቅፍ አድርጎ እንደመሳም አድርጎ ፍቅሩን በመግለፅ ይታወቃል።
ከእድሜ መግፋትና ከሕመም ጋር በተያያዘ ጁፒተር ሰውነቱ በጣም ከሳ።
ጁሊያ በመጨረሻ ከእርሱ ጋር ስትገናኝ ጁፒተር እጅግ ደክሞ ነበር ቢሆንም ግን ወዲያውኑ አውቋታል።
ጁፒተር ምንም እንኳ የመንቀሳቀስ አቅም ቢያጣም ሕይወቱን ሙሉ ከጎኑ የነበረችውን ጁሊያን ለማቀፍና ለመሳም በመሞከር ፍቅሩን ገልጾላታል።
ከዚህ ግኑኝነታቸው ሁለት ቀናት በኋላ በ20 ዓመት ዕድሜው ጁፒተር ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።
ለዘመናት ያሳደገችውን እስከ መጨረሻው እስትንፋሱ ድረስ ያልረሳው ጁፒተር በእንስሳትና በሰዎች መካከል ያለውን ጥልቅ ቁርኝት እንደገና ያሳየ አጋጣሚ ሆኖ አልፏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Colombia #Animals
#sicklion #woman
#affectionate #Júpiter
#passedaway
Source: GetuTemesgen









No comments yet.